የፕሬዝዳንታዊ ስልጣናቸው በግንቦት 2024 የተጠናቀቀው ቮሎድሚር ዜለንስኪ፡ ከህዝባቸው ይልቅ ስልጣናቸውን ማስጠበቅን ይመርጡ ይሆን የሚሉ አንቂ ድምፆች መደመጥ ጀምረዋል። ለመሆኑ ስለዜለንስኪ የዘርፉ ተንታኞች ምን ይላሉ?
''በዩክሬን በስልጣን ላይ ያሉት ሰው የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ግንዛቤያቸው ዝቅተኛ ነው። ስልጣናቸውን አራዝመዋል፤ እናም የዩክሬን ብሄራዊ አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ጠንካራ ቁርኝት እንዲሁም በቀጠናው ሰላምና ደኅንነትን የሚጠብቁ ናቸው ብዬ አላምንም። የፖለቲካ ሳይንስ ለግለሰቦች ከሚሰጠው ብያኔ አንጻር [...] ይህ ሰው አሁንም እያታለለ ገንዘብ እንደሚቀበል አርቲስት ሆኖ ነው የምናገኘው። '' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የእዮብዘር ዘውዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ስለምን ከዩክሬናዊያን ህይወት ይልቅ ለስልጣኑን መቀጠል ግድ ሰጠው ስንል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የእዮብዘር ዘውዴን አወያይተናቸው ምልከታቸውን አጋርተውናል። በክፍል ሁለት ደግሞ በደቡብ አፍሪካ የተቋማት ማሻሻያዎች ራንድ (የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ) በኢኮኖሚያቸው ውስጥ ያለውን አቅም ስለማጎልበቱ 'ፈርስት ናሽናል ባንክ' በተሰኘው የሀገሪቱ የፋይናንስ ተቋም ውስጥ ከፍተኛ ኢኮኖሚስቱ ኮኬትሶ ማኖ የሥራ ክፍላቸውን በመወከል ዕይታቸውን አካፍለውናል።
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox