Continental Drift

አዲሱ የአፍሪካ ሉዓላዊነት ንቅናቄ፡ የሳህል ቀጠና፣ ሩሲያ እና የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም ፍጻሜ

Sputnik
ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር በምዕራባውያን ላይ ያነሱት የሉዓላዊነት ጥያቄ የዓለምን ጂኦ-ፖለቲካ ቀይሮታል። ለዘመናት "ፀረ-ሽብር" በሚል ሽፋን የተካሄደው የሀብት ዘረፋ እና ጣልቃ ገብነት ሲያበቃ፣ ሀገራቱ ፊታቸውን ወደ ሞስኮ አዙረዋል። ለመሆኑ ይህ የሽግግር ወቅት ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ነጻነት እና ለባለብዙ ዋልታ የዓለም ስርዓት ምን ትርጉም አለው?

" የሩሲያና የአፍሪካ ግንኙነት የሚወሰነው በሩሲያና በአፍሪካ መሪዎች ነው። እና ይህ መሰረታዊ ነገር ነው። የሁለቱ ማለትም ሩሲያ እንደ አንድ ሀገር፣ አፍሪካ እንደ ብዙ ሀገር—የሚሰጡት፣ መሪዎቻቸው የሚወስኑት ነገር ወደፊት የሁለቱን ግንኙነት... የሚወስን ይመስለኛል።" ሲሉ በሩሲያ የኢትዮጵያውያን ማህበር ፕሬዝዳንት እና በሩሲያ የስቴት ዱማ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አማካሪ ፕሮፌሰር ዘነበ ክንፉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን (AES) ምስረታን፣ የሩሲያን የ"ያለ ጣልቃ-ገብነት" የአጋርነት መርህ እና የአፍሪካን አዲሱን የነጻነት ትግል በሩሲያ የኢትዮጵያውያን ማህበር ፕሬዝዳንት እና በሩሲያ የስቴት ዱማ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አማካሪ ፕሮፌሰር ዘነበ ክንፉ ጋር በሰፊው ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox