The Rising South

ከጸረ-ቅኝ ግዛት እስከ ስልታዊ አጋርነት፡- በዲፕሎማሲው መስክ የቀጠሉ ሁነቶች

Sputnik
የደቡባዊው ዓለም ሀገራት ከምንጊዜውም በላይ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን ማጠናከር የግድ የሚላቸው ጊዜ ላይ ደርሰዋል፡፡ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት የማእድን ሀብታቸውን ሲሉ በታዳጊ ሀገራት ላይ ቀጥተኛና ህገወጥ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መፈጸም ቀጥለዋል፡፡ “ይህ የተመድ ድክመት ነው። ምክንያቱም እነዚህ አገራት በሙሉ፣ ድሃም ይሁኑ ሀብታም፣ ነፃ አገራት ናቸው። አሜሪካ በእነዚህ አገራት ላይ ጥቃት መፈጸም የለባትም። ይህ የኢምፔሪያሊዝም መገለጫ ነው። በመሆኑም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአንድነት ሊቆም እና በነፃና ሉዓላዊ አገራት ላይ የሚፈጸመውን የጥቃት ድርጊት መቃወም አለበት።” ሲሉ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ግኑኝነት ባለሙያ የሆኑት ዱጋሳ ሙሉጌታ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህ ባለ ሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ ከ ዱጋሳ ሙሉጌታ(ዶ/ር)ጋር በመሆን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የ2026 ዓመታዊ ጋዜጣዊ ማብራሪያቸውን መነሻ አድርገን ሞስኮን ወደ ደቡባዊ ዓለም /Global South/ እያደረገች ያለውን ከፍተኛ ትኩረት እንወያያለን። የቢትኮይን ባለሙያ ከሆነው ቃል ካሳ ጋር የቢትኮይን (Bitcoin) ኢንቨስትመንትን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያን ዲጂታልፋይናንስ ትኩረት መነሻ አድርገን ፣ አማራጩ እውነተኛ የፋይናንስ ሉዓላዊነትን ሊያመጣ ይችላልን? የውጭ ምንዛሪ እጥረትንስ ይቀርፋል? በሚሉት ነጥቦች ዙሪያ ያደረግነውን ውይይት በሁለተኛው የዝግጅት ክፍላች ዳስሰነዋል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox