The Rising South

የሉዓላዊነት ጉዞ፦ ኢትዮጵያ በጤና፣ በምግብ እና በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች እያመጣች ያለችው አዲስ ለውጥ

Sputnik

"የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ባለሥልጣን የደረጃ ሶስት (Maturity Level 3) እውቅናን ማግኘቱ ለሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው፣ እንዲሁም ለእኛ እንደ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጨዋታ ቀያሪ ትልቅ ክስተት ነው።[...]የምስክር ወረቀቱን በቀላሉ በመጠቀም በኢትዮጵያ የተመረተን ማንኛውንም ምርት በመላው አፍሪካ አልፎም ከዚያ በላይ ማሰራጨት እንችላለን።" ሲሉ ፋርማኮሎጂስት እና የኢትዮጵያ የፋርማሲ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በቀዳሚነት 'ፋርማኮሎጂስት' እና የኢትዮጵያ የፋርማሲ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ከሆኑት ከዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ ጋር በኢትዮጵያ የመድኃኒት ዘርፍ መንግስት የገበያውን መጠን እስከ 2030 ድረስ ወደ $3.6 ቢሊዮን ለማሳደግ የሰነቀውን ዕቅድ እንቃኛለን። በመቀጠል የኢትዮጵያን የስንዴ ምርት እድገት ከ ከፍተኛ የግብርና ተመራማሪዉ ጸደቀ አባተ (ዶ/ር) ጋር እናነሳለን። በመጨረሻም በኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ከፍተኛ የአቪየሽን ባለሙያ ከሆኑት ከአቶ እንዳለ ተሾመ ጋር ሆነን ቦይንግ ስለ አፍሪካ አቪየሽን ዕድገት ያስቀመጠውን ትንበያ እና የኢትዮጵያ ልዩ ሚና እንመረምራለን።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox