''የአሜሪካ ዓላማ ቀጠናው እንዳይረጋጋ በማድረግ ፍላጎታቸውን ማሳካት ነው። ኢራቅን ለአብነት ብንወስድ፣ አውዳሚ የጦር መሣሪያ አለ በሚል ሽፋን ጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት ሀገርን ያለምንም ማስረጃ በሴራ ንድፈ ሀሳብ አውድመዋል። በዚህም በራሷ የሚደገፉ የሽብር ኃይላትም ተፈልፍለዋል'' ሲሉ በአፍሪካ ቀንድና መካከለኛው ምሥራቅ ጂዮፖለቲካ ተንታኙ መሃመድ ንጉስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ አሜሪካ በተለያዪ ጊዜያት በመካከለኛው ምሥራቅ ባደረጋቻቸው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶች ምክንያት የተፈጠሩ ቀውሶች በተመለከተ ከ ጂዮግራፈር፣ ካርቶግራፈር እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድና መካከለኛው ምሥራቅ ጂዮፖለቲካ ተንታኙ መሃመድ ንጉስ ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ በአቶሚክ ስኬል ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ ቋት (hub) የማድረግ እንቅስቃሴን በኢትዮጵያ የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ተቋም የናኖ ቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ዘርፎች መሪ የሥራ ኃላፊ ወንድማገኝ ማሞ (ዶ/ር) ጋር ቃኝተነዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox