Continental Drift

የገንዘብ ህትመት በሀገር ውስጥ፡- የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት አዲሱ ምዕራፍ

Sputnik
ኢትዮጵያ የራሷን ገንዘብ ኖት በሀገር ውስጥ የደረሰችው ውሳኔ፣ ከውጭ ኩባንያዎች ጥገኝነት የመላቀቅ እና የገንዘብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ ውሳኔ ከዶላር ጥገኝነት ለመውጣት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በሌላ በኩል Make Africa Borderless Now ''አሁን አፍሪካን ንብር የለሽ እናድርጋት ንቅናቄ'' አህጉሪቱን ትስስር ዕውን ለማድረግ እየሰራ ነው።

"የራስን ገንዘብ ማተም ካልተቻለ ፣ በራስ ገንዘብ መበደር ፣ መገበያየት እና መቆጠብ ካልተቻለ ፤ ሉዓላዊነት እንደ ሀገር አደጋ ላይ ይወድቃል።[...] የራስን ገንዘብ ማተም የራስን ሀገር በራስ አቅም ከማስተዳደር ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው።" ሲሉ መርዕድ ፍቅረዮሐንስ፣ የፕራግማ ኢንቨስትመንት አማካሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ ኢትዮጵያ ገንዘቧን በሀገር ውስጥ ማተም የመጀመር ዉጥኗን ትርጓሜ ከኢንቨስትመንት ባለሙያው መርዕድ ፍቅረዮሐንስ ጋር እንፈትሻለን።እንዲሁም አፍሪካን ለትስስር ማነቆ የሆነውን የድንበር ሀሳብን ስለሚታገለው ንቅናቄ ከጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ባን ዴንግ (ዶ/ር)ጋር እንወያያለን ።

እንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox