''ብሪክስ እንደ አላማ አድርጎ ከተነሳበት መካከል ፋይናንስ፣ኢኮኖሚ፣ንግድ፣የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ንፁህ የአየር ከባቢ መፍጠርና የዲጂታል ሥራዎችን ማስፋፋት ይገኙበታል። እኛ አፍሪካዊያን ነገሮችን በብስለት መምራትና መጠቀም ከቻልን ከብሪክስ የልማት ባንክ ብዙ መጠቀም እንችላለን። የልማት ባንኩ ከቀደመው የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ ጫናም እንድወጣም የሚያስችል ነው።'' ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያና በሩሲያ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶ/ር አሉላ ተክለብርሃን አዲሱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ በንግድ እና ኢኮኖሚ ላይ ያለው በጎ ተፅዕኖ በተመለከተ ከአሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ እና በሩሲያ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶክተር ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ጉዳይን በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድቤት ፊት ስለማቅረብ ከያዛቸው ውድነህ የኢንቫይሮመንታል ጂዮግራፈር፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና አዳፕቲሽን ባለሙያ፣ መምህርና ተመራማሪ ጋር ቃኝተነዋል።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox