"አፍሪካውያን ሉዓላዊነትን የምንገልፅበት እና የምንረዳበት መንገድ ምዕራባውያን በ'ዌስታፋሊያ' ሰምምነት መሰረት ከሚነግሩን የሉዓላዊነት እሳቤ የተለየ ነው።[...] አፍሪካውያን የወረስነውን የምዕራቡን ዓለም ሉዓላዊነት መንገድ በመተዉ [...] ወደውስጥ መመልከት፣ የጋራ ሀብቶቻችንን በጋራ ስለመጠቀም ማሰብ አለብን።" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ዛሬ በድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ጥንቅራችን 'አፍሪካ ሀብቶቿን በጋራ ለመጠቀም ትችል ዘንድ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ያለውን ምዕራብ ተኮር እሳቤ መተው ስትችል ነው' የሚል መከራከሪያ ከሚያቀርቡት እና በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ ያደርጋል። በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ደግሞ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች ጉብኝትና ምክክር መነሻ በማድርግ የአፍሪካ ከተሞችን እና የእድገት ጉዟቸዉን ይዳስሳል። ለዚህም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የመጡ እንግዶች ጋር ቆይታውን ያደርጋል።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts –Deezer – Afripods –Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts –Deezer – Afripods –Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox