ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ምርቶች ለማንቀሳቀስ ስታቅድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ የአፍሪካን የአቪዬሽን ታሪክ የሚቀይር ግዙፍ የኤርፖርት ፕሮጀክት ጀምሯል። እነዚህ የአየር እና የየብስ መሰረተ ልማቶች ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና ለአፍሪካ ትስስር ያላቸው ፋይዳ ወሳኝ ነው፣የኢኮኖሚ ዞኖችም ቁልፍ ሚናን ይጫወታሉ።
"ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ማዕከላዊ ሚና መጫወት አለባት። ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ኢትዮጵያን የአፍሪካ ማኑፋክቸሪንግ እና የሎጂስቲክስ ማዕከል እንድትሆን ይረዱናል።[...]የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ስምምነትን በመጠቀም ያለንን አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት መቀየር አለብን።" ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን የኢትዮጵያን የኢንደስትሪ ልማትና ከአህጉራዊ የነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት ተጠቃሚነት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ጋር እንመለከታለን። አዲሱ የኤርፖርት ፕሮጀክት ለአፍሪካ አቪዬሽን ያለውን ፋይዳም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ያስተላለፉትን መልእክት እንቃኛለን።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox