The Rising South

ሀገር በቀል ሳይንስ፦ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና የወደፊቱ የእውቀት አመራር

Sputnik
“የብሪክስ ሀገራት ተሰባስበው በብዙ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው። የብሪክስ አካዳሚዎች ማህበር፣ የሳይንስ ማህበራት እና ሌሎችም አሉ። ይህ ደግሞ የበለጠ መቀጠል አለበት። አሁን ያለው ገና በጅማሮ ወይም በጨቅላነት ደረጃ ላይ ነው። ይህ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማደግ እና ወደ ተግባር መለወጥ ይኖርበታል።” ሲሉ ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የኢትዮጵያን የሳይንስ እና የልማት ምኞቶች ቁልፍ ሚና የሚጫወተው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚን በትኩረት እንቃኛለን። የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ ፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ የራሷ ምሁራዊ መሰረት በመነሳት ምርምርን፣ ፈጠራን እና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ቀረፃን ለማጎልበት ስላለው ተልዕኮ እንወያያለን፡፡ በተጨማሪም አካዳሚው ሀገራዊ እድገትን እንዴት እየቀረጸ እንደሆነ፣ ከብሪክስ ሀገራት ጋር ያለውን ጨምሮ ዓለም አቀፍ አጋርነቶችን እንዴት እየገነባ እንደሆነ፣ እንዲሁም በግብርና፣ በአየር ንብረት መቋቋም፣ በትምህርት እና በሌሎችም ዘርፎች ላይ የሚያደርጋቸውን ለውጥ አምጭ እንቅስቃሴዎች እንቃኛለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox