Drum of Changes

ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩ፦ ለፓን አፍሪካኒዝም እና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ምን ዋሉ ?

Sputnik
"አባቴ፣ ለኢትዮጵያ ከአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን የተሻለ አጋር የለም ብሎ ያምን ነበር … አባቴ በአሜሪካን ሀገር በትምህርት ላይ ሳለ ጥቁር በመሆኑ ብቻ የደረሰበትንም አልረሳም … እነዚህ ሁኔታዎች የፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ላይ እንዲበረታ አድርገዉታል"- ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬዉ ድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ታላቁን ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩን እንዘክራለን። ለዚህም በቅርቡ "ከተማ ይፍሩ፡ የሰላም፣ የእድገት እና የአፍሪካ አንድነት ሻምፒዮን" በሚል ርዕስ አባታቸዉን የሚዘክር መጽሐፍ ያሳተሙት ልጃቸው አቶ መኮንን ከተማ ይፍሩ እንግዳችን ናቸው። ሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ፣ በቅርቡ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከበረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጉዳዩ አድርጎታል። ለዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የኢትዮጵያ ታሪክ እና ማህበረሰብ ጥናት ማዕከል ኃላፊ የሆኑትን ዘላለም ተፈራን (ዶ/ር) አነጋግረናል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerAfripods Spotify Pocket Casts Podcast Addict CastBox