Continental Drift

የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ እንቅስቃሴ በአፍሪካ፡- 'ኢትዮ ፔይ' ከዶላር ጥገኝነት ነጻ ለመሆንና ለፋይናንስ ሉዓላዊነት

Sputnik
የ'ኢትዮ-ፔይ' መጀመር ኢትዮጵያ በዶላር ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥናል። በሌላ በኩል፣ ሚሊዮኖች የኤሌክትሪክ ብርሃን ባልታደሉበት አፍሪካ፣ የኢነርጂ አቅርቦትንና ብቃትን ማሳደግ ወሳኝ የቤት ሥራ ሆኗል።
"በዶላር ላይ ጥገኝነት አይኖርም [...]ቴክኖሎጂው ክፍያዎች በቀላሉ እንዲተላለፉ ያስችላል። ነገር ግን ወደ ተግባራዊ ትግበራው ስንመጣ፣ የሕግ ማዕቀፍ ጣልቃ ገብነት ያስፈልገዋል። በህግ በኩል፣ ሁለቱ ሀገራት ክፍያው እንዴት እንደሚፈጸምና የገንዘብ ምንዛሪው እንዴት እንደሚሆን መስማማት አለባቸው።" ሲሉ የኢት-ስዊች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ 'ኢትዮ-ፔይ' ስለሚፈጥረው ዕድል ከኢት-ስዊች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ጋር እንወያያለን። ቀጥለን የአፍሪካን የኢነርጂ እንቅፋቶችን ከ'ሰስተነብል ኢነርጂ ፎር ኦል' የኢነርጂ ብቃት ባለሙያ ኤልዛቤት ዋንጌሲ ቼጌ እና ከደቡብ አፍሪካ የኤሌክትሪክ እና ኢነርጂ ምክትል ሚኒስትር ሳማንታ ግራሃም-ማሬ ጋር እንፈትሻለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox