Continental Drift

ኃይል፣ ወደብ እና ቅርስ፡- የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ እና የሉዓላዊነት ትግል

Sputnik
የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ቀጠና በጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ናቸው። እስራኤል ለሶማሌላንድ የሰጠችው ዕውቅና፣ የሁቲ አማጽያን ዛቻ እና ከእስራኤል ጋር የገብበት ፍጥጫ ቀጥሏል፡፡ በሌላ በኩል፣ ከመቅደላ የተዘረፉ ቅርሶቻችንን ከብሪታኒያ ሙዚየም "በብድር" ሳይሆን በክብር የመመለስ ትግል የአፍሪካዊያን ሌላ ሜዳ ሆኗል።

"እስራኤል ለሶማሌላንድ ስትራቴጂካዊ ቦታ እና አስፈላጊነት ትኩረት እየሰጠች ነው፤ ምክንያቱም ሁቲዎች በእስራኤል ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ኢላማዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው።" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት መሰናዶ የሶማሌላንድ የሀገርነት እውቅናና ትርጓሜውን ከፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ጋር እንፈትሻለን። ተዘርፈው ለእይታ የሚቀርቡበት የብሪታኒያ ሙዚየም ቅርሶችን "በውሰት" ለአፍሪካ ሀገራት የመስጠት እቅድና የተዘረፉ ቅርሶችን የማስመለስ ሂደት የትግል መልክን በተመለከተም ከቅርስ አስተዳደር እና ጥበቃ ከፍተኛ ተመራማሪ ተስፋዬ አራጌ ጋር እንወያያለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox