“የኢትዮጵያ አየር ኃይል በጣም በጣም ታላቅ ተቋም ነው። ሶማሊያ ስትወረን፣ ከምሥራቅ አቅጣጫ 700 ኪሎ ሜትር የሚሆነውን መሬታችንን ይዘው ነበር። የኢትዮጵያ አየር ኃይል በመልሶ ማጥቃት ትልቅ ትምህርት ወራሪውን ኃይል ያስተማረበት ወቅት ነበር። በኢትዮጵያ አየር ኃይል በዚያ በሚገባ በተደራጀውና ከፍተኛ ዲሲፕሊን በነበረው ድርጅት እኮራለሁ።” የኢትዮጵያ አየር ኃይል የቀድሞ አባል ካፒቴን ኢንጂነር አበበ ከበደ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ አንጋፋ አርበኛ ከሆኑት ከካፒቴን ኢንጂነር አበበ ከበደ ጋር በመሆን አየር ኃይሉ የአህጉራዊ ጥንካሬ ደረጃ ላይ እንዴት እንደደረሰ፣ ራሱን የቻለ እና በቴክኖሎጂ የላቀ ኃይልን ለመገንባት ምን እንደሚያስፈልግ የተወያየን ሲሆን፤ ደራሲ እና ተመራማሪ እንዲሁም የእውቁ ዲፕሎማት የከተማ ይፍሩ ልጅ ከሆኑት ከመኮንን ከተማ ይፍሩ ጋር በአዲሱ የ “ጋዝ ባይ ሬይል” ኢኒሼቲቭ ላይ ተመስርተን የአፍሪካን የኢነርጂ ሉዓላዊነትን፣ ከቅኝ አገዛዝ ነጻ የሆነ ልማትን እና አፍሪካ የራሷን ችግሮች ለመፍታት መገንባት ስላለባት ተቋማት ያደረግነው አጭር ቆይታም በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ተዳስሷል፡፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ :
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ :
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox