የ12ኛው የአንድሬ ስቴኒን ዓለም አቀፍ የፕሬስ ፎቶ ውድድር በሞስኮ ተከፈተ

Sputnik
ሞስኮ ( RIA ኖቮስቲ.) የ12ኛው የአንድሬ ስቴኒን ዓለም አቀፍ የፕሬስ ፎቶ ውድድር በሞስኮ በይፋ ተከፍቷል ፤ የተወዳዳሪዎችን ማመልከቻ መቀበል ጀምረዋል። እ.ኤ.አ በ2014 ክረምት በዶኔትስክ አቅራቢያ በተገደለው የሮሲያ ሴጎድኒያ ሚዲያ ቡድን የፎቶ ጋዜጠኛ የነበረው የአንድሬ ስቴኒን መታሰቢያ የሚካሄደው ዓመታዊው ውድድር፣ እንደተለመደው በልደቱ ቀን ታህሳስ13 ተጀምራል።

ዲሚትሪ ኪሴሌቭ፣ የሮሲያ ሴጎድኒያ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ቡድን ዋና ዳይሬክተር፡

“ለ12ኛ ጊዜ የአንድሬ ስቴኒን ውድድር ማመልከቻዎችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነው፣ ይህ ሁሌም አስደሳች እና የሚያጓጓ ወቅት ነው። በተለይ ይህ ዓመት ልዩ ነው፣ ተሳታፊዎችን እንደሚያስደስት እርግጠኞች የሆንንበትን አንድ አስገራሚ ነገር አዘጋጅተናል። እድሜያቸው 34 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ የፎቶ ጋዜጠኞችም ‘ኢነርጂ ኦፍ ላይፍ’ የተዘሰኘውን አዲስ ምድብ በደስታ እናበስራለን። የእኛ ተልዕኮ ሳይለዋውጥ አዳዲስ ስሞችን የማግኘት እና ለወጣት ፎቶግራፍ አንሺዎች ጠንካራ ጅምር በመፍጠር አሁን ድረስ ቀጥሏል። በተመሳሳይ ፣ ለቀጣዩ ትውልድ መመዘኛዎችን የሚያስቀምጡ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ሥራ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት አለን። ከልምድ ካላቸው አንጋፋዎችም ሆነ ብቅ ካሉ ባለሙያዎች የሚመጡ ፕሮጀክቶችን በጉጉት እንጠብቃለን – በአንድነት ሆነው የዘመናዊ የፎቶ ጋዜጠኝነትን የተለያየ፣ ሕያውና አንዳንዴም እርስ በእርስ የሚጋጭ ገጽታ ይፈጥራሉ። የዚህ ሂደት አካል በመሆናችን ኩራት ይሰማናል።”

ምድቦች እና የመግቢያ ውሎች

ውድድሩ ስድስት ምድቦችን ያካትታል፡ ‘ቶፕ ኒውስ’ ፣ ስፖርት፣ ‘ማይ ፕላኔት’ ፣ ‘ፖርትሬት.የዘመናችን ጀግና’ ፣ የከፍታ እይታ ወይም ‘ቶፕ ቪዉ’እና አዲስ የተዋወቀው ‘ኢነርጂ ኦፍ ላይፍ’ ምድቦች ናቸው።
በ‘ቶፕ ኒውስ’ ፣ ‘ማይ ፕላኔት’ እና ‘ፖርትሬት.የዘመናችን ጀግና’ ምድቦች ውስጥ የሚገቡ የመወዳደሪያ ምስሎች በነጠላ ምስል ወይም በተከታታይ ፎቶዎች ለውድድር መቅረብ ይቻላል። የስፖርት እና የከፍታ እይታ ወይም ‘ቶፕ ቪዉ’ምድቦች ነጠላ ምስሎችን ብቻ ይቀበላሉ።
‘ኢነርጂ ኦፍ ላይፍ’ ምድብ እድሜያቸው 34 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ፎቶግራፍ አንሺዎች ክፍት ሲሆን፣ ቀሪዎቹ አምስት ምድቦች ደግሞ ከ18 እስከ 33 ዓመት ለሆኑ ተሳታፊዎች ክፍት ናቸው።
‘ፕሮፌሽናል ፎቶግራፍ’ አንሺዎች ማመልከቻዎችን በውድድሩ ኦፊሴላዊ ድህረ ገጽ በሩሲያኛ(stenincontest.ru) እና በእንግሊዝኛ (stenincontest.com) እስከ የካቲት 21፣ 2017ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
ለ2025 ውድድር የሽልማት ፈንድ በእያንዳንዱ ምድብ ለመጀመሪያ ደረጃ 125,000 ሩብልስ፣ ለሁለተኛ ደረጃ 100,000 ሩብልስ እና ለሶስተኛ ደረጃ 75,000 ሩብልስ ይሰጣል። የውድድሩ ከፍተኛ ክብር ተቀባይ፣ ግራንድ ፕሪክስን ያሸነፈው 700,000 ሩብልስ ይቀበላል። የ12ኛው የአንድሬ ስቴኒን ዓለም አቀፍ የፕሬስ ፎቶ ውድድር ሽልማት ሥነ ሥርዓት በ2019 ዓ.ም መጀመሪያ በመስከረም እና ህዳር ወር መካከል በሞስኮ እንዲካሄድ ታቅዷል።

የተከበሩ ዳኞች እና ታዋቂ አሸናፊዎች
ባለፉት ዓመታት የውድድሩ ዳኞች ቭላድሚር ቪያትኪን (ሩሲያ)፣ ገብርኤል ሴኮኒ (ጣሊያን)፣ ሴፋ ካራካን (ቱርክ) እና ሁዋን ካኔቴ (አርጀንቲና)ን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ፎቶግራፍ አንሺዎችን ተሳትፈውበታል።
የአሸናፊዎች ዝርዝር በዓለም ታዋቂ የሆኑ የፎቶ ጋዜጠኞችን ያካትታል፤ ከእነዚህም መካከል በሴቶች እስር ቤቶች ላይ በሰራችው ተከታታይ ስራዋ የምትታወቀው የየሌና አኖሶቫ (ሩሲያ)፤ የሽባ ሴት ልጅን ሕይወት በሚዘግበው "ሌቲዚያ፡ የማይታይ ሕይወት ታሪክ" ለተባለው ስራው ሽልማት የተሰጠው ዳኒሎ ጋርሺያ ዲ ሜኦ (ጣሊያን)፤ እና በቤልግሬድ ስላሉ ስደተኞች በሰራው ዘገባ የተከበረው አሌሃንድሮ ማርቲኔዝ ቬሌዝ (ስፔን) ይገኙበታል። እ.ኤ.አ. በ2025 የውድድሩ ግራንድ ፕሪክስ የጦር አርበኞችን ጉዳትና የስሜት ቀውስ ቢኖርባቸውም በሰላማዊ ሕይወታቸው ውስጥ ድፍረትንና ታጋሽነትን ማሳየታቸውን በሚያሳይ "የሩሲያ ባህሪ፡ የመሰናክል ጨዋታ" ለተሰኘው ተከታታይ ስራዋ ለየካተሪና ያከል (ሩሲያ) ተሰጥቷል።
የዘንድሮው ውድድር አሸናፊ ስራዎችን በሩሲያ እና በውጭ ሀገር በሚደረጉ ጉዞዎች ኤግዚቢሽኖች በማሳየት የቆየ ባህሉን ይቀጥላል። ባለፉት 12 ዓመታት የውድድሩን አሸናፊ ፎቶግራፎች የሚያሳዩ ኤግዚቢሽኖች ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሜክሲኮ፣ አርጀንቲና፣ ኡራጓይ፣ ኮሎምቢያ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ቱርክ፣ ሊባኖስ፣ ጀርመን፣ ስፔን፣ ጣሊያን፣ ግሪክ፣ ሃንጋሪ፣ ፖላንድ፣ ግብፅ እና ሌሎችም በርካታ አገሮች ቀርበዋል።
ስለ ውድድሩ
የአንድሬ ስቴኒን ዓለም አቀፍ የፕሬስ ፎቶ ውድድር የሚዘጋጀው ፣ በሩሲያ ፌዴሬሽን የዩኔስኮ ኮሚሽን አስተባባሪነት በሮሲያ ሴጎድኒያ ሚዲያ ቡድን ሲሆን ፣ ወጣት ፎቶግራፍ አንሺዎችን ለመደገፍ እና ዘመናዊ የፎቶ ጋዜጠኝነት የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች በተመለከተ የህዝብ ግንዛቤን ለማሳደግ ያለመ ነው።
የውድድሩ አጠቃላይ የሚዲያ አጋሮች VGTRK (የሁሉም-ሩሲያ ግዛት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ብሮድካስቲንግ ኩባንያ) እና የሩሲያ የኦንላየን ፕላትፎርም SMOTRIM ናቸው።
የውድድሩ ዓለም አቀፍ የሚዲያ አጋሮች ኢንዲፔንደንት ሚዲያ ሆልዲንግ እና ኤኤንኤ የዜና ወኪል (ደቡብ አፍሪካ)፤ ሻንጋይ ዩናይትድ ሚዲያ ግሩፕ(SUMG) እና ዘ ፔፐር ኦንላየን ፖርታል (ቻይና)፤ ዳር አል ሻርቅ ሚዲያ ሆልዲንግ (ኳታር)፤ ብራሲል247 የኦንላየን ፖርታል (ብራዚል)፤ ፒቲአይ የዜና ወኪል (ህንድ)፤ አይአይኤንኤ የዜና ወኪል (ኢራቅ)፤ ሜህር የዜና ወኪል (ኢራን)፤ ኤንኤኤን የዜና ወኪል (ናይጄሪያ)፤ እና ሺንዋ የዜና ወኪል (ቻይና) ይገኙበታል።
የውድድሩ ኢንዱስትሪ አጋሮች የሩሲያ ጋዜጠኞች ህብረት፣ የወጣት ጋዜጠኞችየመረጃ ፖርታል እና ‘ፎቶ-ስተዲ. አርዩ’ ወይም Photo-study.ru (ሩሲያ) ናቸው።