The Rising South

የታሪክ ባለቤትነት እና የይዞታ ፍትሕ በአፍሪካ

Sputnik
“ዓላማችን መሆን ያለበት የአፍሪካ ወጣቶችን አእምሮ ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ነፃ ማውጣት ነው፤ ምክንያቱም ባለፉት ጥቂት መቶ ዓመታት የአፍሪካ ታሪክ ሲታጠብና ሲበረዝ ቆይቷል። [...]ስለሆነም፣ አሁን ባለው የግዙፍ የሃሳብ ለውጥ ወቅት፣ ታሪካችን ከአፍሪካ ነፃነት ጋር እንዳልተጀመረ በአፍሪካም ሆነ በመላው ዓለም ለሚገኙ ወጣቶች የማሳወቅ፣ የማስተማር እና ግንዛቤ የመፍጠር ኃላፊነት የኛ ነው።” ሲሉ የቱሪዝም ባለሙያ እና የባህል ጉዳዮች አንቂ ራስ አብይ ጥላሁን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው ባለሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ የቱሪዝም ባለሙያ እና የባህል ጉዳዮች አንቂ ራስ አብይ ጥላሁን አፍሪካውያን ቅርሶቻቸውን እና ግዛቶቻቸውን ለንግድ መጠቀሚያ ከሚያደርጉ ሥርዓቶች ታሪካቸውን እንዴት መልሰው እየተረከቡ እንደሆነ እንዲሁም ስለ አፍሪካ አንድነት፣ ስለ ታሪካዊ ንቃት እና ባህልን ማዛባት ስለሚያስከትለው አደጋ በሰፊው ተወያይተናል፡፡ በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፣ ከታሪክ ባለቤትነት ወደ መሬት ፍትሕ ተሻግረን ስላልተቋጨው የአፍሪካ የመሬት ባለቤትነት እና የሉዓላዊነት ትግል ከደቡብ አፍሪካ የመሬት ማሻሻያ እና የገጠር ልማት ሚኒስትር ምዝዋኔሌ ኞትሶ፣ የዚምባብዌ መሬት ኮሚሽን ሰብሳቢ ቴንዳይ ሩት ዎከር እና የክዋሜ ንክሩማ ዩኒቨርሲው ፕሮፌሰር ሩዲዝ ኪንግ ጋር ቆይታ እናደርጋለን።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox