የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ90-95 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ የባህል ቅርሶች ከአህጉሪቱ ውጭ ይገኛል። በዋና ዋና የአውሮፓ ሙዚየሞች ብቻ ከ500,000 በላይ የአፍሪካ ቅርሶችን ይዘዋል። ከእነዚህም ውስጥ ብዙዎቹ በቅኝ ግዛት ዝርፊያ፣ በአስገዳጅ ሁኔታዎች ወይም በሕገ-ወጥ ዝውውር የተገኙ ናቸው።
"ከአገራችን ተዘርፈው ተወሰዱ ቅርሶቻችን በክፍያ መልሰን እንድንወስድ መጠየቃችን አሳዛኝ ነገር ነው። እነዚህን ቅርሶች የያዙ ሙዚየሞች ወይም የግል ቅርስ ሰባሳቢዎች ወደኢትዮጵያ እንዲመልሷቸው እናበረታታለን"ሲሉ የሺ ካሳ፣ የራስ ደስታ ዳምጠው የልጅ ልጅ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አባተ ጎበና (ዶ/ር) በበኩላቸው
"በመቅደላ ጦርነት ወቅት ወደኢትዮጵያ የመጡ እንግሊዛውያን፣ አስቀድመው ስለኢትዮጵያ ውድ ቅርሶች ያውቁ ነበር። እነዚህን ቅርሶችም ለመዝረፍ በጀት ተመድቦላቸው የመጡ ታዋቂ ባለሞያዎችም የሀገሪቱ ቅርሶች ዘርፈው ወጥተዋል [...] በተለያየ መልኩ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ምዕራባዉያን በማንኛውም አጋጣሚ ባዶ እጃቸውን የሚወጡበት አጋጣሚ አልነበረም፡፡" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው ልዩ የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በምእራቡ ዓለም እስረኛ የሆኑት የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ቅርሶችን ጉዳይ እንመረምራለን፡፡
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts –Deezer – Afripods –Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox