Sovereignty Sources

ነገን አሻግሮ መመልከት፡ ኢመርጂንግ ሳይንስን ከፈጠራ ጋር የማዋሃድ ጥረት

Sputnik
''ዓለም ውስጥ እንደመሆናችን ቴክኖሎጂ ተቀባይ ብቻ መሆን የለብንም፣ ቢያንስ ግንዛቤው ሊኖረን ይገባል። የምንቀበለው ምንድነው የሚለውንም ማወቅ ይገባል — ኢመርጂንግ ሳይንስ ለእያንዳንዱ ችግሮቻችን መፍትሔ የሚስጥ ስለሆነ ከዓለም ወደኋላ መቅረት የለብንም [...] ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ሳይንስ ለምሳሌ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የግብርና ዘርፍን ሊያጎለብት ይችላል '' ሲሉ በባዮ እና ኢመርጂንግ ኢንስቲትዩት የኢመርጂንግ ማዕከል ውስጥ አስተባባሪና ተመራማሪው ዶ/ር ከበደ ጋሞ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል::
በፕሮግራሙ ክፍል አንድ በባዮ እና ኢመርጂንግ ኢንስቲትዩት በኢመርጂንግ ማዕከል ውስጥ አስተባባሪና ተመራማሪው ዶ/ር ከበደ ጋሞ ምንነቱን፣ ከፈጠራ ጋር ለማስተሳሰር የሚደረገውን ጥረት፣ የዘርፉን መጎልበት፣ ቁልፍ ሚናውን ከሌሎች ቁልፍ ነጥቦች ጋር በማስተሳሰር ሙያዊ ሀሳባቸውን ያጋሩናል። ከአውቶሞቲቭ ጋዜጠኛው እዮብ ሞገስ ጋር የመንገድ ትራፊክ አደጋ እየፈጠረ ስላለው የማኅበራዊና ምጣኔ ሐብታዊ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ የተደረገው ውይይትም የፕሮግራሙ ሌላኛው አካል ነው።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox