“አፍሪካ ቢያንስ 100 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ [በዓመት] ምግብ ለማስገባት ታወጣለች። ይህ የግብርና ዘርፍ ሊለውጠው ይችል ነበር። ስለዚህ [...] መንግስታት በዋና ዋና መሠረተ ልማቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ አለበት። ከእነዚህም መካከል መስኖ ቁጥር አንድ ሊሆን ይችላል፤ ሜካናይዜሽን ደግሞ ቁጥር ሁለት፤ የገበያ መሠረተ ልማት ደግሞ ቁጥር ሶስት ነው። ” ሲሉ የአሊያንስ ፎር ግሪን ሪቮሊዩሽን አፍሪካ ዳይሬክተር እና የ2025 የአፍሪካ የግብርና ባለራዕይ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን አመዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የአሊያንስ ፎር ግሪን ሪቮሊዩሽን አፍሪካ ዳይሬክተርና የ2025 የአፍሪካ የግብርና ባለራዕይ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን አመዴ ጋር ስለ አፈር ጤና እና አፍሪካ ወደ ዘላቂ የምግብ ሥርዓቶች የምታደርገውን ጉዞ እንፈትሻለን። በሁለተኛው ክፍልም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር እመቤት በቀለ(ዶ/ር ) ፣ የአፍሪካ ቱሪዝም ቦርድ ዋና ጸሐፊ ሂወቴ አሰፋ፤ እና የዲቦራ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤኪ አባዱላ —የሴቶችን አቅም ማጎልበት፣ ሩሲያ-አፍሪካ ትብብርና ተያያዥ ጉዳዮች ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox