The Rising South

ከቅድመ አያቶች ጥበብ እስከ ጤና ሉዓላዊነት፡ አፍሪካ ለፍትሕ የምታደርገው ትግል

Sputnik

“የቅኝ ገዥዎች ልጆቻችንን ማሠልጠን ጀመሩ። እኛ እንደ ሕዝብ በአእምሯችን ውስጥ ልጆቻችንን የሚያሠለጥኑልን ለእኛ መስሎን ነበር። ግን የሚያሠለጥኗቸው ለራሳቸው ነበር። እና ልጆቹን ለራሳቸው እያሠለጠኑ መሆናቸውን የተረዳንበት ጊዜ፣ በጣም ዘግይቶ ነበር። አሁን በእኛና በልጆቻችን መካከል ክፍተት መጣ።” ሲሉ የአፍሪካ ቴስት ድርጅት ተባባሪ መስራች ተንጎል ክፕለማኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ።

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ በቅኝ ግዛት የተናጋውን የአፍሪካን ባህላዊ ማንነት እና የሞራል መሰረቶችን /የቅድመ አያቶች ጥበብ/ እንዴት መልሶ ማቋቋም እንደሚቻል የኮንጎ እና የዛምቢያ የብዊሌ ህዝቦች ንጉስ ከፍተኛ መሪ ፑታ ስምንተኛ ፣ በአዲስ አበባ የኤስዋቲኒ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን ኃላፊ አንቶይኔት ሄንዉድ ሮናልድ እና የአፍሪካ ቴስት ድርጅት ተባባሪ መስራች ተንጎል ክፕለማኒን አነጋግረናቸዋል፡፡ ከንግድ ጋር የተያያዙ የአእምሯዊ ንብረት መብቶች ገጽታዎች ስምምነቶች እና የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ሕጎች የአፍሪካን አህጉር የፈጠራ እና ሕይወት አድን መድኃኒቶች ተደራሽነት ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ የቮለንቲር ኸልዝ ሰርቪስስ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፍቃዱ ጋር ያደረግነው ውይይትም በሁለተኛው ክፍል ይዳሰሳል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox