ኪን-ኢትዮጵያ የጥበብና ባህል ጉዞ ኢትዮጵያን ለዓለም የማስተዋወቅ ዓላማ አድርጎ ብሪክስ አባል ሀገራት እያቀረበ ነው፣ በቻይና እና ሩሲያ ስራዉን ያቀረበው ቡድኑ፣ በቅርቡም ወደ ብራዚል ያቀናል ፡፡
''ኪን - ኢትዮጵያ ትልቅ የባህል፣ የጥበብ እና የዲፕሎማሲ፣ የብዙ የኪነጥብ ባለሙያዎች ስብስብ ነው። ኅብረትን መሠረት ያደረገ ሥራ በመሥራታችን ውጤቱ እጅግ የሚደነቅ ነው [...] ብሪክስ የዓለምን ሚዛንን ለማስተካከል የተፈጠረ አቅም ስለሆነ አባል መሆናችን በብዙ ይጠቅመናል።'' ሲል የኪን ኢትዮጵያ ቡድን መሪ፣ አሰልጣኝና ድምፃዊ ወንድዬ አበበ (ወንድዬ ኮንታ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል ።
ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ ኪን ኢትዮጵያ ቡድን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደረገ ያለው ጉዞ በብሪክስ ማዕቀፍ ስር የባህል ዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ለመወያየት የኪን ኢትዮጵያ ቡድን መሪ፣ አሰልጣኝና ድምፃዊ ወንድዬ አበበ (ወንድዬ ኮንታ) በእንግድነት ጋብዘነዋል። በክፍል ሁለት ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ የፊልም ስራዎች ጠልቀን ፣ ዘርፉ ለአንድነት እና ቀጠናዊ ትስስር ስላለው ሚና ከዳይሬክተር፣ ኤዲተርና ፕሮዲውሰር ክብሮም በርሄ ጋር የተደረገው ቆይታ ያደርጋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox