''አፍሪካ የተለያዩ የተፈጥሮ ኃብት አላት። ይህ ደግሞ ለኢንዱስትሪያላይዜሽን ሂደት ትልቅ አስተዋፅዖ ቢኖረውም ቅኝ ግዛት የምጣኔ ሀብት እድገት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥሮ አልፏል። ይህ ደግሞ እንደ ትልቅ ጫና የሚቆጠር ነው።'' ሲሉ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንታል ስተዲስ መምህሩ ፍራፊስ ሀይሉ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሶቨርኒቲ ሶርስስ ሁለት ጉዳዮችን በሚዳስስበት በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ አፍሪካ በኢንዱስትሪ ራሷን ስለመቻል እና የምጣኔ ሀብት ሉዓላዊነትን ስለሚፈጠርበት ጉዳይ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ስተዲስ መምህሩ ፍራፊስ ሀይሉን (ዶ/ር) አነጋግሯቸዋል። በክፍል ሁለት ከምዕራባዊያን እርዳታ ተላቅቆ የውስጥ የማሪታይም ተቋምን መሠረት በማድረግ ስለሰማያዊ ኢኮኖሚ በዚሁ ፕሮግራም በክፍል ሁለት የኢትዮጵያ ማሪታይም የስልጠና ተቋም የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የስልጠና ልማት ኃላፊ ስዩም ትዕግስቱ ጋር የተደረገው ቆይታም ሌላኛው ጉዳያችን ነው።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡