Drum of Changes

የአፍሪካ ቀጣናዊ ጥምረቶች ፣ የአህጉር አቀፍ ትስስር ካስማዎች ወይስ ወጥመዶች?

Sputnik
"አፍሪካ የገንዘብ ሀብት እጥረት እንደሌለባት ልብ ማለት ያስፈልጋል - አፍሪካውያን የጎደለን የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት የሚሆን ፍላጎት ነው። በእውነት የሚያስፈልገን ተቋማዊ አቅምን ለማጎልበት የሚያስችል ቁርጠኝነት ነው። የዚህ ዓይነቱ ቁርጠኝነት ስለጎደለንም ልብ በሚሰብር መልኩ ከውጭ በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ላይ ጥገኛ ሆነን ቀርተናል" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርስቲ መምህርና የፓን አፍሪካ አስተሳሰብ እና ውይይት ተቋም ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ እና የአስተዳደር እና የአፍሪካ ውስጥ የንግድ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ድራም ኦፍ ቼንጅስ በዛሬው ዝግጅቱ ሁለት የተለያዩ ግን ወሳኝ ጉዳዮችን በስፋት ይዳስሳል፡፡ አህጉሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ቀጣናዊ ጥምረቶች ለአህጉር አቀፍ ትስስር ካስማዎች ናቸው ወይስ በውስን የፋይናንስ አቅማቸው ምክንያት አፍሪካን የማጥመጃ መረብ ሆነዋል? ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት በደቡብ አፍሪካ በሚገኘው በጆሃንስበርግ ዩኒቨርስቲ መምህርና የፓን አፍሪካ አስተሳሰብ እና ውይይት ተቋም ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ እና የአስተዳደር እና የአፍሪካ ውስጥ የንግድ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) አነጋግረናቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ 'በአረቡ ዓለም ፖለቲካ በተሳሳተ መንገድ እንድትሳልና ብሔራዊ ጥቋንም ለማስከበር' የአረብ ሊግ ሊሆን ቀጣይ የጥምረት መዳረሻዋ እንዴት ሊሆን እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ምክለታቸውን አጋርተውናል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ።