Continental Drift

ፍትህ በችሎት ላይ: የአፍሪካ ድምፆች ከአለምዓቀፍ የወንጀለኞች ባሻገር

Sputnik
ፍትህ የውጭ ተጽዕኖን ሲከናነብ ፣ ማን ይዳኛል ፣ ማንስ ደግሞ በነጻ ይለቀቃል?
''የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ምስረታን ስንመለከት፣ አብዛኞቹ ለክስ የሚቀርቡ ጉዳዮች የአፍሪካ ጉዳዮች ሆነው እናገኛቸዋለን። በአህጉር አቀፍ ደረጃ ለጦርነቶች አስተዋጽኦ የሚያደርጉት አብዛኞቹ ሀገራት ግን የአፍሪካ ሀገራት አይደሉም። ስለዚህ እንደ አፍሪካውያን የዉስጥ ጉዳዮቻችንን የምናይበት የአፍሪካ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የምናቋቁምበት ጊዜ አሁን እንደሆነ አምናለሁ። ራሳቸውን ከአይሲሲ ቻርተር ያገለሉትን የአፍሪካ ሀገራትንም ማድነቅ ወይም ማመስገን እወዳለሁ'' ስትል የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ዋና ጸሐፊ ግሎሪያ ሲሲያ ምማሲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች።
በዚሁ የኮንቲነንታል ድሪፍት መሰናዶ ሁለት የተለያዩ ግን ወሳኝ ጉዳዮችን እናያለን፣ አፍሪካዊያን ለምዕራባዊያ ባደሩ የ'ፍትህ ተቋማት ስለሚፈጸምባቸው በደልና እና የአፍሪካ ሀገራት አማራጮች ምንድን ናቸው ስንል የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች የቀድሞ ተመራቂዎች ኮሚሽን ፌዴሬሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር አልፍሬድ ኤሊ፣ የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ዋና ጸሐፊ ግሎሪያ ሲሲያ ምማሲን እና የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን የሰሜን አፍሪካ ክልላዊ ዳይሬክተር ራታኒያ ዳዊን ጠይቀናል፡፡ በሌላኛው ጉዳያችን ደግሞ የአፍሪካ የግብርናና ገጠር ልማት ጦችን ለማስመዝገብ አፍሪካ ምን ማድረግ አለባት ስንል የኢንተር አፍሪካ ፊቶሳኒተሪ ካውንስል አስተባባሪ ዶ/ር ሳሊዩ ኒያሲ፣ የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቫላካቲ እና ሌሎችንም አነጋግረናቸዋል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ይከታተሉ