''ለአካባቢ ጉዳይ የየሀገራትን ድርሻ በህግ መወሰን ይጠይቃል። ይህ ከሌለ ሦስቱም ሀገራት ሆኑ ሌሎቹ በዘላቂነት መንገዶቻቸውን ሊያቀኑ አይችሉም። የውኃ ክፍፍል ወይም መጋራት የሚባለው በህግ መመሥረት አለበት — ኃብት ባጠረ ቁጥር እኔ እለቅልሃለሁ፤ አልጎዳህም ብቻ በማለት ሀሳባቸው ሊረጋ አይችልም "- ሲሉ ሀይድርሎጁስቱ፣ የውኃ ሐብቶች መሃንዲስና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪው ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ተናግረዋል።
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተገናኘ የሚነሱ አንኳር ዲፕሎማሲዎችና የባይንዲንግ አግሪመንት ጉዳዮች የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢ ከሀይድሮሎጂስት ፣ የውኃ ሀብቶች መሃንዲስና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪው ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ጋር ተወያይቷል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Afripods – Deezer – Pocket Casts – Podcast Addict – Spotify