The Rising South

"ኮሬክት ዘ ማፕ" ፣ አፍሪካን በዓለም ካርታ ላይ በትክክለኛ የስፋት መጠኗ ለማስፈር የሚደረግ ዘመቻ

Sputnik
“የአፍሪካን ትክክለኛ መጠንና ስፋት በጣም በሚቀንስ መልኩ ያንን ምስላዊ ውክልና ያለማቋረጥ ማየቱ፣ በእርግጥ በጂኦፖለቲካ፣ በባለሀብቶች፣ አፍሪካን በሚመለከቱበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።" የአፍሪካ ኖ ፊልተር የአድቮኬሲ እና የእንቅስቃሴ መሪ ሎራቶ ሞጎአት
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በአፍሪካ ' ኖ ፊልተር እና ስፒክ አፕ አፍሪካ' የሚመራውን "ኮሬክት ዘ ማፕ" ዘመቻን እና አፍሪካ በዓለም ካርታ ላይ እና በዓለም አቀፍ ትርክት ውስጥ ትክክለኛ ቦታዋን እንድታገኝ የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንቃኛለን።
ለውይይታችን የአፍሪካ 'ኖ ፊልተር የአድቮኬሲ' እና የእንቅስቃሴ መሪ ሎራቶ ሞጎአት እና የስፒክ አፕ አፍሪካ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ያሲን ጂቦ ሰፊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ጋብዘናቸዋል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify