ባሳለፍነው ሳምንት በአላስካ የተካሄደው ጉባኤ በታሪክ ተመራማሪዉ ፕሮፌሰር አየለ በክሪ ገለፃ የአውሮፓውያን እና የዩክሬንን እንቅፋቶችን ተሻግሮ የተከናወነ ነው። ውይይቱ ግን ለዓለም አቀፍ ስጋቶችም መፍትሄ የመሆን ተስፋን የሰጠ ነው።
በሩሲያ እና በአሜሪካ የሚደረግ ስምምነት ሌሎች ዓለም አቀፍ ስጋቶችን ለመፍታት እንደ ማዕቀፍ ሊያገለግል ይችላል -ፖለቲካ ሳይንስ እና የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ባለሙያ በፍቃዱ ዳባ
በዚህኛው የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን የፕሬዝደንት ፑቲን እና የፕሬዝደንት ትራምፕን የአላስካ ስብሰባ በጥልቀት እንዳስሳለን። የመሪዎቹን ዉይይት ቀጣይ ተፅዕኖዎችንም በተመለከተ የታሪክ ምሁርና ተመራማሪዉ ፕሮፌሰር አየለ በክሪ ፣ የሕ/ ተ/ ም/ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር ) ፣ የፖለቲካ ሳይንስ እና የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ባለሙያ በፍቃዱ ዳባን አነጋግሯቸዋል፡፡