''የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ ቦታዎች ላይ ቢፈጠርም በአብዛኛው ከባህር ወይም ከውቅያኖስ በታች የሚፈጠር ነው፡፡ አትላንቲክ ውስጥ አለ፣ ህንድ ውቅያኖስ ውስጥ አለ፣ ልዩ ልዩ ቦታ አለ፡፡ በደንብ ግን የመፈጠሩ ሂደት የሚታየው ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ሰምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው።''
የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መሠናዶው በርዕደ መሬት እና ተያያዥ ጉዳዮች ሙያዊ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ተመራማሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ጋብዟቸዋል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Afripods – Deezer – Pocket Casts – Podcast Addict – Spotify