“እኛ ምን ያቅተናል?፣ ሀገራችንን ለማሳደግ ምን ያቅተናል?፣ ማይንድሴት /አመለካከት/ ላይ መስራት አለብን ፤ የሁሉም ማይንድሴት ላይ መሰራት አለበት ምክንያቱም [ከሌሎች ሃገራት ተወዳዳሪዎች ጋር] አቅማችን አንድ እንደሆነ አይቻለው፡፡” ተማሪ አቤል ደረጀ
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በጄኔቫ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውድድር ኢትዮጵያን በኩራት ወክለው 5ኛ ደረጃን ከያዙ ከተማሪ አቤል ደረጄ እና ፍሬወይኒ በላይነህ እንዲሁም ከውድድሩ የኢትዮጵያ ተወካይና አስተባባሪ መንግስቱ ወዳጄ ጋር ቆይታ እናደርጋለን፡፡ በወጣቶች ዘንድ ሰው ሰራሽ አስተዉሎትን ለበጎ የመጠቀም ውድድር አጠቃላይ ሂደቱን፣ የጄኔቫ ቆይታቸው እና ስላገኙት ተሞክሮም ውይይት አድርገናል፡፡