The Rising South

የጤፍ ባለቤትነት፦ የኢትዮጵያ ትግል ከብዝሃ-ህይወት ሃብት ዘረፋ ጋር  

Sputnik
የአፍሪካ ሼፎች ጉባኤ እና የሥርዓተ ምግብ የፖሊሲ ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፤ ጉባዔው ማጠንጠኛ ካደረገባቸው ጉዳዮች አንዱ የምግብ ሉዓላዊነት ይገኝበታል፡፡ ይህን ከሚፈታተኑ ተግባራት ውስጥም በምዕራቡ ዓለም ኩባንያዎች የሚፈጸሙ የ'ባዮፓይሬሲ' ወይም የብዝሃ- ህይወት ሃብት ዘረፋ አንዱ ነው፡፡
“የብዝሀ ሕይወት ዘረፋ 'ባዮፓይሬሲ' ለደቡባዊ  ዓለም ሀገራት አሳሳቢ ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት  በተፈጥሮ የአዝርዕት ዘረመል ሀብት የበለፀጉ ናቸው። የሰሜኑ ዓለም ሀገራት ኩባንያ ባለቤቶች ግን እነዚህን የአዝርዕት ዘረመል ሀብቶችን ለመጠቀም [በራሳቸው ስም ለማስመዝገብ] ፍቃድ እየጠየቁ ነው። […] የአዝርዕት ሉዓላዊነት በጣም ወሳኝ ነው፣ ምክንያቱም የተለያዩ ዘሮች በእጃቸው ከሌሉ የምግብ ዋስትና አይኖርም።”
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት አቅራቢው ኢትዮጵያ ጤፍ ላይ የተፈፀመባትን የባለቤትነት ዘረፋ መነሻ አድርጎ የተፈጥሮ ሃብት ዘረፋ የ'ባዮፓይሬሲ'ን ዓለም አቀፍ ኢፍትሃዊነት በሰፊው ይዳስሳል፤ የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ሥርዓቶች እና የአግሮኢኮሎጂ ኮንሰርቲየም ዋና ዳይሬክተር ባዩሽ ፀጋዬ (ዶ/ር) ጋብዟቸዋል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify