የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ የድምፅ አስተውህሎት በተለይም በሠው ሠራሽ አስተውህሎት የሚታገዘው መተግበሪያ እንዴት የአፍሪካን ቋንቋዎች በዲጂታል መንገዱ ተደራሽና እጅግ ጠቃሚ እንደሚያደርግ፣ በዘርፉ የሀገራት ተሞክሮና እንደ ሩሲያ ካሉ በዘርፉ የመጠቁ ሀገራት ጋር የሚደረግ ትብብር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ሀሳቦች በጥልቀት ለመወያየት ቅዱስ ያሬድ፣ የሀሳብ ኤ አይ - የድምፅ ሠው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያ ተባባሪ መሥራችን ጋብዞታል።
በቴክኖሎጂ እና የሠው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ሩሲያ ለኢትዮጵያ የምታጋራው በርካታ አቅሞች አሏት። የሚደረጉ የልምድ ልውውጦችም ለኢትዮጵያ ሁነኛ አቅም ይሆናሉ።
“ከፍተኛ የትብብር አቅም አለ። በሁለቱ አገራት መንግስታት መካከል በኒውክለር ኢነርጂ፣ ቴክኖሎጂና የሠው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፎች የአጋርነት ስምምነቶች ይገኛሉ። ይህ ደግሞ በመሠረታዊነት የረጅም ጊዜ የግንኙነት እና አጋርነት ነጥብ ነው። በዚህ ረገድ ከሩሲያ በርካታ የምንማራቸው ነገሮች አሉ። ይህም መሥራት የምንችለውን ነገር ነው የሚያሳየው'' ሲል የሀሳብ ኤ አይ ተባባሪ መስራች ቅዱስ ያሬድ ተናግሯል።
ቅዱስ በዘርፉ ስላሉ መጠነ ሰፊ ድጋፎች ሲያብራራ፦
“በጎለበተ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በማደግ ላይ ለሚገኙ አገራት ዋናው ጉዳያቸው በመሠረታዊ ደረጃ ያለ መሠረ ልማት። ከኤሌክትሪክ ሲቲ እና ኢንተርኔት ተነስቶ እስከ ዳታ ማዕከል እና ተቋማት የሚደርስ ነው። ይህም በግል ዘርፉ የሚደገፍ ነው። በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ እየተመለከትነው ያለነው የሠው ሰራሽ አስተውሎት ተቋም እና ኢንሳ የግል ዘርፉን ለማሳተፍ የሚያደርጉት ጥረት የሚበረታታ ነው'' ሲል ተናግሯል።
በቆይታችን የተነሱ ቁልፍ ነጥቦች
በሠው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀጉ ሀገርኛ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ረቂቅ ችግሮችን ይፈታሉ።
ዓለም አቀፍ ትብብሮች፣ እንደ ሩሲያ ካሉ ሀገራት ጋር የሚደረግ አጋርነት የገበያ ትስስርን ሲፈጥር በዘርፉ አቅምን ያጎለብታል።
የበለጠ ለመረዳት ይፈልጋሉ? ይህንኑ አጠቃላይ የሠው ሠራሽ አስተውሎት፣ ቴክኖሎጂና ዲጂታል ሉዓላዊነትን በተመለከተ የሚዳስሰውንና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም ይከታተሉ!