The Rising South

የብሪክስ ሪዮ መግለጫ፦ ተጨባጭ የኃይል ሽግግር

Sputnik
በብራዚሏ መዲና ሪዮ ዴ ጄኔሮ የተካሄደው የ2025 የብሪክስ ጉባኤ ለደቡባዊው ዓለም ትልቅ ለውጥ ያመጣል። የብሪክስ ሀገራት የፋይናንስ ነፃነትን፣ የተባበሩት መንግስታት ማሻሻያን እና የቴክኖሎጂ ማካተትን የሚጠይቅ 126 ነጥቦችን የያዘ ሰፊ መግለጫ በማውጣት የዓለምን ሥርዓት በመቀየር ላይ መንገዳቸው ቀጥለዋል።
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) እንዲህ ይላሉ፦
የብሪክስ አባል ሀገራት የራሳቸውን የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) ይፈጥራሉ። [...] አዲሱ የልማት ባንክ ለብሪክስ ልማት ማዕከል ይሆናል። [...] ምዕራባውያን ብዙ የኃይል ማዕከላት እንዳሉ ከመገንዘብ ውጪ ሌላ አማራጭ አይኖራቸውም — ይህ ሌላ ቀዝቃዛ ጦርነትም አይደለም''፣ ብለዋል።
ብሪክስ በዉስጡ የያዘው ከአሳታፊነትም በላይ የሆነ የእኔነት ትርጉም ያለው ተሳትፎ እና እኩል የመደመጥ እድልም አፍሪካ ፊቷን ወደዚህ ጥምረት እንድታዞር አድርጓታል።

አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ለብድር አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀምጣሉ። የብሪክስ ብድሮች ቅድመ ሁኔታዎችን ይቀንሳሉ። [...] የአፍሪካ አጀንዳ እና የብሪክስ አጀንዳዎች በጣም ተመሳሳይ ናቸው ወይም የጋራ አሰላለፍ አላቸው። ለዚህም ነው ብሪክስ የአፍሪካን አጀንዳ፣ የአፍሪካን ችግር፣ ለአፍሪካ ችግር የአፍሪካ መፍትሔ የሚያበረታታው።” ሲሉ ይጥና ገብሬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የብሪክስን መነሳት እና ለአፍሪካ እና ለተቀረው ዓለም ምን ማለት እንደሆነ የሚዳስሰውን ይህን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ዝግጅት ይከታተሉ።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify