አፍሪካ ከምትጠቀመው ክትባት በራሷ የምታመርተው 1% ብቻ መሆኑን ያውቃሉ?
የአህጉሪቱ የጤና ደህንነት መሠረት ያደረገው የውጭ ድጋፍ ላይ እንደመሆኑ እርምጃ የመውሰጃ ጊዜው አሁን ነው!
የሶቨርኒቲሶርስ ፕሮግራም በዛሬው መሠናዶው በክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች ሀሳባቸውን እንዲያጋሩን በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጨቅላ ህፃናት ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ጡረኝ ስዩም ን ጋብዟቸዋል።
ዶ/ር ጡረኝ ሀገር በቀል ክትባት ማምረት የሚያስፈልግበት ምክንያትን ሲያስረዱ፡
“ክትባት በብዙ መጠን ማምረት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ምክንያቱም አቅርቦት አለመኖር ከማነቆዎች መካከል አንዱ ስለሆነ። ስለዚህ፣ በራሳችን አውድ የክትባት ምርት ሊኖረን ይችላል ነገር ግን ብዙ ሥራዎች ፣ ኢንቨስትመንት እና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ነው።” ሲሉ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ሀገራት በጋራ ተጣምረው ክትባት ማምረት ስለሚችሉባቸው መንገዶች ዶ/ር ጡረኝ ሲያብራሩ :-
“የአፍሪካ ሀገራት አንድ ላይ በመሆን ይህን ችግር መፍታት እንችላለን። ነገር ግን ምንም እንኳ አንድነት ብንፈጥርም፣ በቁርጠኝነት የረጅም ጊዜ የጋራ መግባባት የሚፈልግ ጉዳይ ነው። እናም እንደጠቀስኩት ለክትባት ምርትና ልማት ብዙ መመዘኛዎች አሉ። ስለዚህ ግቦቹን ለማሳካት እነዚያ ሁሉ መመዘኛዎቾ ሊታቀዱና ሊሰሩ ይገባል።'' ብለዋል።
➡️ የጅምላ ምርት - እጥረትን ለመቅረፍ
➡️ የፓን አፍሪካ ትብብር - ለረጅም ዘመን ስኬት
➡️ ኢንቨስትመንትና ቁርጠኝነት - ራዕይን ወደ እውነታነት ለመለወጥ
ስለሀገር በቀል ክትባት ምርት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የበለጠ ለመረዳት ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበዉን ፣ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ሙሉ ፕርግራምን ይከታተሉ።
ሙሉ ፕርሮግራሙን ለማድመጥ ዝግጁ ነዎት?