የአፍሪካ የዕዳ ጫና ከጠቅላላ የአህጉራዊ ምርት ውስጥ ከ 66 በመቶ በላይ ሆኗል ። ለዚህም ደካማ የብድር ስርዓት እና ሙስና ምክያቶቹ ናቸው፡፡ ይህ የጤና ስርዓት ላይ እና ትምህርትን በማደናቀፍ ረገድም አሉታዊ ሚናን እየተጫወተ ነው።
በዛሬው የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን ከኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የጋበዝናቸዉ ዶ/ር ጀማል መሐመድ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ።
📝 “ብድር በግድ ውሰዱ ብለው አያስወስዱንም፡፡ [...] ከጀርባ ግን ብድር እንድንጠይቅ የሚገፋፉ ነግሮች አሉ ፡፡ ወርልድ ባንክም አይ ኤም ኤፍም፡፡ [...] በተለይ አፍሪካ አካባቢ ደግሞ ይህንን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተቋማት ስለሌሉ አብዛኛው [ብድር] በካፒታል ፍላይት [ብድሩ በሃገር ስም ቢመጣም] ብሩ ተመልሶ ወደ አዉሮፓ እና አሜሪካ ይሄዳል፡፡ በተመሳሳይ [ዕዳዉን] እኛ እንከፍላለን ፣ አበዳሪዎች ያተርፋሉ" ብለዋል፡፡
የምስራቃዊ ቡድን አቀራረቦችን በተመለከተም ዶ/ር ጀማል መሐመድ:-
🌏 "የሩሲያ እና የቻይና አቀራረብ በምጣኔ ሃብታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በተለይ የሩሲያ አቀራረብ ከዚያ በላይም ሊሄድ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ከነጻነት ትግል ወቅት ጀምሮ ሀገራት ነጻ እንዲሆኑ ሃቀኛ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩት ሩሲያዎች ናቸው፡፡ እስካሁን ያላቸው እሴት ይመስለኛል፡፡ [...] ሌሎቹም አገራት የእነሱን ዓርዓያነት ተክትለው ነበር፡፡ ለአብነት ኩባን መጥቀስ ትችላለህ፡፡ እነ ፊደል ካስትሮ ለኢትዮጵያ እና አንጎላ ድጋፍ ያደረጉት [ለዚያ ነው]” ሲሉ ተናግረዋል።
🔑 ዶ/ር ጀማል እንደ መፍትሄ ባሉት ሀሳብ:-
"አፍሪካውያን እንደመሆናችን መጠን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በማጠናከር የውጭ ኃይሎች ላይ ጥገኝነትን መቀነስ አለብን። 54 የተለያዩ ኢኮኖሚዎች ያሏት አፍሪካ ታሪፎችን እና የገበያ እንቅፋቶችን በማስወገድ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን የሚስብ አንድ ወጥ ገበያ መፍጠር ትችላለች" ብለዋል፡፡
ስለ አፍሪካ የእዳ ጫና እና ከእዳ መውጫ መንገዶች ለማወወቅ ይህንን የ ራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ይከታተላሉ።