የኤሌትሪክ ኃይልን በመጠቀም ከብክለት የጸዳ የትራንስፖርት ማዕከል ለመሆን የሚደረግ ኢትዮጵያዊ ጉዞ!
🎙በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት የትራንስፖርት ባለሙያው አቶ ሞገስ ነጋሽ ኢትዮጵያ ከፖሊሲ እስከ ትግበራ ድረስ በትራንስፖርት ረገድ የያዘችውን ጉዞ ፣ እንዲሁም በኬንያ ስለሚካሄደው አውቶኤክስፖ ከቡርኪናፋሶ እና ናይጀሪያ የተሽከርካሪ ምርት ስኬት ጋር አያይዘው ስለ አፍሪካ አረንጓዴ ጉዞ ሀሳባቸውን አጋርተውናል። 🌍
"በኢትዮጵያ ውስጥ ርካሽ የሰው ኃይል አለ... የፀሐይ ብርሃን፣ መልክዓምድራዊ አቀማመጡን ስትመለከት ኢትዮጵያ የቃጣናውን የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ምርት በበላይነት ለመምራት የሚያስችላት ትልቅ ዕድል አለ።"
"ኢትዮጵያ ተሽከርካሪን ከመገጣጠም አልጀመረችም....አሰቀድመን መማር ነበረብን። ሥልጠናውን ጋገኘን በኋላ ግን አሁን ላይ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን እየገጣጠምን ነው። ስለ ኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎችም ሥልጠና ብናገኝ፣ አቅሙም ፣ ልምዱም እንዲሁም የተማረ የሰው ኃይል ስላለን የሚከብደን አይደለም።" በማለት አክለዋል።
ኢትዮጵያ ስለተያያዘችው የኃይል ለውጥ የበለጠ ለማወቅ ይህንን የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ይከታተሉ።🔌🌿