የሩሲያ-አሜሪካ የኤክስፐርቶች ቡድን ንግግርን በተመለከተ ክሬምሊን በሰጠው መግለጫ የተነሱ ቁልፍ ነጥቦች፦ የጥቁር ባህር ስምምነት፦ ሁለቱም ወገኖች የባህር ላይ ደህንነትን ለማረጋገጥ፣ የንግድ መርከቦችን ለወታደራዊ ጥቅም ማዋልን ለመከላከል እና የፍተሻ ዘዴዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል። የሩሲያን የግብርና ንግድ ማመቻቸት፦ የሩሲያ ባንኮችን ከስዊፍት ጋር ማገናኘትን ጨምሮ የፋይናንስ እና የንግድ ክልከላዎችን በማንሳት ሩሲያ የግብርና እና ማዳበሪያ ምርቷን ለዓለም አቀፍ ገበያ ማቅረብ እንድትችል ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ እንደምታደርግ ቃል ገብታለች። የጥቁር ባህር ስምምነት ትግበራ ቅድመ ሁኔታ፦ የስምምነቱ ትግበራ በሩሲያ የግብር ባንክ ሮስልኮዝባንክ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ሲነሳ ይጀምራል። የኢነርጂ መሠረተ ልማት ተኩስ አቀም፦ ሩሲያ እና አሜሪካ ከመጋቢት 9 ጀምሮ በሩሲያ እና በዩክሬን የኃይል ተቋማት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን ለ30 ቀናት ለማቆም ተስማምተዋል። አንደ ስምምነቱ አተገባበር ቀኑ ሊራዘም ወይም ሊቀር ይችላል። የሶስተኛ ወገን ሽምግልና፦ ሁለቱም ሀገራት በኃይል እና በባህር ደህንነት ላይ የተደረጉ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ዓለም አቀፍ ድጋፍን በደስታ ይቀበላሉ። የሰላም ቁርጠኝነት፦ ውይይቶቹ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ሰላም ለማምጣት የተጀመረውን ጥረት እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል። የባህር ትራንስፖርት ኢንሹራንስ ወጪን መቀነስ፦ አሜሪካ የባህር ትራንስፖርት ኢንሹራንስ ወጪን በመቀነስ የወደቦች ተደራሽነትን ለማስፋት ትሠራለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን