አሜሪካ የሩሲያ የግብርና ምርት እና ማዳበሪያ ወደ ዓለም ገበያ እንዲመልስ እገዛ ታደርጋለች ሲል ኋይት ሀውስ በሪያድ የተካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ የመግለጫው ተጨማሪ ነጥቦች፦ ▪ዩናይትድ ስቴትስ ለሩሲያ የማዳበሪያ እና ምግብ ኤክስፖርት ወደብ እና የክፍያ ስርዓት ለማመቻቸት አቅዳለች።▪አሜሪካ እና ሩሲያ በጥቁር ባህር ደህንነቱ የተጠበቀ ጉዞ ለማረጋገጥ እና ኃይል ከመጠቀም ለመቆጠብ ተስማምተዋል። ▪አሜሪካ እና ዩክሬን በጥቁር ባህር የንግድ መርከቦች ላይ የሚወሰደውን የኃይል እርምጃ ለማስቀረት ተስማምተዋል። ▪ዋሽንግተን እና ኪዬቭ በሩሲያ እና በዩክሬን የኢነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን የሚያስቀር መፍትሄ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን