በዩክሬን የሰላም ስምምነት ዙሪያ ሩሲያ እና አሜሪካ በሳዑዲ አረቢያ የሚያደርጉት ውይይት ቁልፍ ጉዳዮች፦ በዩክሬን ግጭት አፈታት ዙሪያ በሩሲያ እና በአሜሪካ የባለሙያ ቡድኖች መካከል በሚደረገው ውይይት ላይ ለመሳተፍ የሩሲያ ልዑካን ቡድን በሳዑዲ አረቢያ መዲና ሪያድ ገብቷል። የሩሲያ ተወካዮች፦ 🟠 የፌዴሬሽን ምክር ቤት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ ግሪጎሪ ካራሲን፣🟠 የፌዴራል ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊ አማካሪ ሰርጌ በሴዳ። የአሜሪካ ልዑካን ቡድን፦ 🟠 በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማርኮ ሩቢዮ ሥር የፖሊሲ እቅድ ዳይሬክተር ሚካኤል አንቶን፣🟠 የፕሬዝዳንት ትራምፕ የዩክሬን ልዩ መልዕክተኛ ጆሴፍ ኬሎግ ረዳቶች፣🟠 ከብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚካኤል ዋልትስ ፅህፈት ቤት የተውጣጡ አባላት። የውይይት ርዕሶች፡- 🟠 ሩሲያ እና አሜሪካ እ.አ.አ ከ2022-2023 ሥራ ላይ ውሎ የነበረውን እና ከዩክሬን ወደቦች ደህንነቱ የተጠበቀ የእህል ኤክስፖርት ኮሪዶር የመፍጠር ዓላማ ያነገበውን የጥቁር ባህር የእህል ተነሳሽነት በድጋሚ ማስጀመር።🟠 በጥቁር ባህር ላይ "ሁለቱም ወገኖች እህል እና ነዳጅ ማጓጓዝ እና የንግድ ልውውጥ መቀጠል እንዲችሉ" በቀረበው የባህር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ውይይቱ እንደሚያተኩር ዋልትዝ ተናግረዋል።🟠 "የጦር የግንባሩ፣ የሰላም ማስከበር" እና "ለዘላቂ ሰላም መሬትን የተመለከተ ውይይት" እንደሚኖር ዋልትዝ ለሲቢኤስ ገልፀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን