ኢትዮጵያ ለኬንያ በቀን 200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ለኬንያ በቀን 200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች ነው ተባለ የኢትዮ-ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ኮንቨርተር ጣቢያ ምስራቅ አፍሪካን በኃይል ለማስተሳሰር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።ከኢትዮጵያ እስከ ኬንያ በተዘረጋ 1 ሺህ 60 ኪሎ ሜትር የማስተላለፊያ መስመርና 2 ሺህ ሜጋ ዋት ኃይል የመሸከም አቅም ባላቸው ሁለት ፖሎች ኃይል እየተላለፈ እንደሚገኝ ተቋሙ ገልጿል። ከኬንያ ጋር በተደረሠው የኃይል ሽያጭ ስምምነት መሠረት በአሁኑ ወቅት በቀን 18 ሰዓት 200 ሜጋ ዋት ኃይል እየቀረበ ይገኛል ተብሏል። ጣቢያው ወደ ታንዛኒያ ኃይል ለማስተላለፍ የተያዘውን ዕቅድ ማሳካት የሚያስችል አቅም እንዳለውም ነው የተገለፀው።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
Sputnik