በሰሜን ተራሮች የዋልያዎች ቁጥር እያሽቆለቆለ እንደመጣ ተነገረ በሺዎች ይቆጠር የነበረው የብርቅዬ ዋልያ ቁጥር ወደ 300 ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታውቋል። በአካባቢው ባለው የፀጥታ ችግር ሳቢያ የቁጥጥር መቀነስ፣ የእሳት አደጋና የሕገ-ወጥ አደኖች መበራከት የዋልያ ቁጥር እንዲመናመን ምክንያት ነው ተብሏል። ብርቅዬው ዋልያ አይቤክስ ከዚህ በፊት አደጋ ላይ መውደቁን ተከትሎ በተሠራ የእንክብካቤ ሥራ ቁጥሩ አንድ ሺህ መድረስ ችሎ እንደነበር ተገልጿል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን