ቱርክ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ ማዕከል ለማቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት አቀረበች

ቱርክ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ ማዕከል ለማቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት አቀረበች የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን ጋር የፕሮጀክቱን ፋይናንስ ምንጭ በተመለከተ ምክክር አድርገዋል። ፕሮጀክቱ በተርኪሽ ትራንስፕላንት ፋውንዴሽን፣ ተርኪሽ ኮኦፖሬሽን ኤጀንሲ እና ኢተርናሽናል ትራንስፕላንት ኔትወርክ እንደሚደገፍ ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የሚሰጠውን የህዋስ፣ ህብረህዋስ፣ እና የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ አገልግሎትን ለማስፋፋት እንደሚረዳ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ ብሔራዊ ሰውነት የአካል ንቅለ-ተከላ ማስተባበሪያ ማዕከልን ማቋቋም፣ የአካል ንቅለ-ተከላ ማዕከል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መመሥረት፣ የሰውነት አካል-ንቅለ ተከላ ሲሙሌሽን ማሰልጠኛ ማቋቋም እና የባለሙያዎች ስልጠናን እንዳካተተ ተነግሯል። @sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
Sputnik