በአፍሪካ እየጨመረ የመጣው የስፑትኒክ ተፅዕኖ እንዳሳሰበው የአውሮፓ የውጭ አገልግሎት ገለጸ የአውሮፓ ሕብረት የዲፕሎማሲ አገልግሎት ሪፖርት የስፑትኒክ አፍሪካ የፈረንሳይኛ ይዘት ዓለም አቀፍ ተደራሽነት እና ተፅዕኖ አየጨመረ መጥቷል ብሏል። ሪፖርቱ "የአውሮፓ ሕብረት እ.አ.አ 2022 አርቲ እና ስፑትኒክ ላይ እገዳ ከጣለ በኋላ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ" ጠቁሟል። "ይህ ዝንባሌ ሩሲያ በግልጽ የሚዲያ ተፅዕኖ አቅጣጫ የመቀየር እና በአንድ ክልል ውስጥ ያሉ ገደቦችን ለማካካስ ሌላ ቦታ ተጽዕኖዋን ማጠናከር እንደምትችል ያሳያል" ሲል ሪፖርቱ ገልጿል። የሩሲያ መንግሥት በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ በሩሲያ ሚዲያ ላይ የተጣለው እገዳ ፖለቲካዊ ሳንሱር እንደሆነና የአውሮፓ ባለስልጣናት "የተቃውሞ ድምጽ የማፈን ፖሊሲያቸውን" እያጠናከሩ መምጣታቸውን ደጋግሞ ይገልጻል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን