ኢትዮጵያ ለሚገጥሟት አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያግዛል የተባለ "የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” ልታቋቁም ነውረቂቅ ሕጉ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበ ሲሆን ፈንዱ “በቅድመ አደጋ፣ በአደጋ እና በድህረ አደጋ ወቅቶች” ሀገሪቷ ለምትወስዳቸው “የአደጋ ስጋት ቅነሳ፣ ምላሽ እና መልሶ ማቋቋም” ተግባራት የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።አዋጁ ለፈንዱ የሚሆን ገንዘብ ከሚሰበሰብባቸው ምንጮች ውስጥ የመንግሥት እና የግል ድርጅት ተቀጣሪ ሠራተኞች ከሚከፈላቸው የተጣራ ደመወዝ ላይ የሚታሰብ ገንዘብ ይገኝበታል። በተጨማሪም ከዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት፣ ቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ከነዳጅ ሽያጭ አቅራቢ ድርጅቶች እና ሌሎችም ለፈንዱ የሚሆን ገንዘብ እንድሚሰበሰብ በረቂቅ ሕጉ ተቀምጧል፡፡ፈንዱን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበላይነት ይመራዋል ተብሏል፡፡@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን