ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛሉጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፓርላማ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፦ ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ8.4 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች።በድምሩ በዚህ ዓመት ከ7 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር ያላነሰ በስንዴ ሰብል ተሸፍኗል፤ ኢትዮጵያ አሁን ላይ በስንዴ ምርት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች። ኢትዮጵያ ከቡና ወጪ ንግድ ባለፉት ስምንት ወራት 1.2 ቢልዮን ዶላር ዋጋ ያለው ኤክስፖርት አድርጋልች፤ በበጅት ዓመቱ መጨረሻ ቁጥሩ 2 ቢልየን ዶልር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱ አየር ማረፊያ ግንባታ በሚቀጥሉተ 6 ወራት ይጀመራል። ኢትዮጵያ 3.5 ቢሊየን ዶላር የእዳ ሸግሸግ ማድረግ ችላለች።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን