ደቡብ አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን ግንኙነት ማሻሻል "ቅድሚያ" የምትሰጠው ጉዳይ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ተናገሩ “ከአሜሪካ ጋር ያለንን ግንኙነት ማሻሻል ለኛ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው፤ ዩናይትድ ስቴትስ ከቻይና በመቀጠል ሁለተኛዋ ትልቅ የንግድ አጋራችን ነች" ሲሉ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በትላንትናው እለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ከአሜሪካ እንዲወጡ መወሰኑን ማሳወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ ውሳኔው አምባሳደር ኢብራሂም ራሶል በበየነ-መረብ ሴሚናር ላይ ባደረጉት ንግግር የትራምፕን አሜሪካ ቅድሚያ ንቅናቄ “በዩናይትድ ስቴትስ እያደገ ላለው የሥነ-ሕዝብ ስብጥር የነጭ የበላይነት ምላሽ” ሲሉ መግለጻቸውን ተከትሎ የመጣ ነው። ራማፎሳ በንግግራቸው “በዩናይትድ ስቴትስ በተለይም በተሰጠው አስተያየት ዙርያ የተንጸባረቀውን ቅሬታ ተገንዝበናል" ብለዋል፡፡በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን