የሶማሊያ ፕሬዝደንት አጃቢ መኪኖች የቦምብ ጥቃት ደረሰባቸው

የሶማሊያ ፕሬዝደንት አጃቢ መኪኖች የቦምብ ጥቃት ደረሰባቸውጥቃቱ የተፈጸመው ከፕሬዝዳንቱ ቤተ-መንግሥት የተነሳ ተሽከርካሪ ወደ ሞቃዲሾ አየር ማረፊያ እያመራ በነበረ ወቅት እንደሆነ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የጸጥታ ኃይሎች በአደጋው ስፍራ መድረሳቸው ተዘግቧል፡፡በጥቃቱ ቢያንስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሶስት ሰዎች የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል ተብሏል።የሶማሊያው መሪ ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው የሶማሊያ ጋርዲያን አረጋግጧል። ፕሬዝዳንቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ሀገሪቱ ግንባር አካባቢዎች በሄሊኮፕተር እንደተወሰዱ ተገልጿል፡፡አሸባሪው አልሸባብ* ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።* በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገሮች የታገደ አሸባሪ ድርጅትበእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
Sputnik
የሶማሊያ ፕሬዝደንት አጃቢ መኪኖች የቦምብ ጥቃት ደረሰባቸውጥቃቱ የተፈጸመው ከፕሬዝዳንቱ ቤተ-መንግሥት የተነሳ ተሽከርካሪ ወደ ሞቃዲሾ አየር ማረፊያ እያመራ በነበረ ወቅት እንደሆነ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የጸጥታ ኃይሎች በአደጋው ስፍራ መድረሳቸው ተዘግቧል፡፡በጥቃቱ ቢያንስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሶስት ሰዎች የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል ተብሏል።የሶማሊያው መሪ ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው የሶማሊያ ጋርዲያን አረጋግጧል። ፕሬዝዳንቱ በአሁኑ ወቅት  ወደ ሀገሪቱ ግንባር አካባቢዎች በሄሊኮፕተር እንደተወሰዱ ተገልጿል፡፡አሸባሪው የአል-ሻባብ* ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።* በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገሮች የታገደ አሸባሪ ድርጅትበእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን