የሰላም ሚኒስቴር የአፋር እና ሱማሌ ክልሎችን የመቀራረብ እና የዘላቂ ሰላም ግንባታ ጥረት እንደሚያበረታታ ገለጸ

የሰላም ሚኒስቴር የአፋር እና ሱማሌ ክልሎችን የመቀራረብ እና የዘላቂ ሰላም ግንባታ ጥረት እንደሚያበረታታ ገለጸ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ ኢድሪስ በትላንትናው እለት በሰመራ በተካሄደው የአፋር እና የሱማሌ ክልል ሕዝቦች የጋራ የኢፍጣር መርሃ-ግብር ላይ የተናገሩት ነው።የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የተጀመረው የአብሮነትና የወንድማማችነት መንገድ ይጠናከራል ማለታቸውን የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በበኩላቸው፤ የሁለቱ ክልሎች ሕዝቦች በርካታ የሚያስተሳስሯቸው ጉዳዮች መኖራቸውን ገልጸው፤ ትስስሩን የበለጠ የሚያጠናክሩ የልማትና የሰላም ግንባታ ሥራዎች በትኩረት እንደሚከናወኑ ተናግረዋል፡፡ ከቀናቶች በፊት ተመሳሳይ የጋራ የኢፍጣር ፕሮግራም በጅግጅጋ ከተማ ተዘጋጅቶ ነበር። በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቆምና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል ስምምነት መደረሱ ይታወሳል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
Sputnik