ሩሲያ በዩክሬን ግጭት አፈታት ሂደት ጠንካራ የደህንነት ዋስትና ትፈልጋለች ሲሉ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ

ሩሲያ በዩክሬን ግጭት አፈታት ሂደት ጠንካራ የደህንነት ዋስትና ትፈልጋለች ሲሉ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ አሌክሳንደር ግሩሽኮ ከኢዝቬስቲያ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ እነዚህ ዋስትናዎች የዩክሬንን ገለልተኝነት እና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ሀገራት ዩክሬንን የሕብረቱ አባል አድርጎ አለመቀበልን ማካተት አለባቸው ብለዋል። እ.አ.አ በ2021 መገባደጃ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአሜሪካ እና ኔቶ የደህንነት ዋስትና የሚጠይቅ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ይፋ አድርጓል፡፡ ረቂቅ ሰነዱ የኔቶን ወደ ምስራቅ መስፋፋት፣ የዩክሬን ህብረቱን መቀላቀል እና እ.ኤ.አ ከ1997 ጀምሮ የተደረገውን የወታደሮች እና የጦር መሳሪያዎች መስፋፋት ይቃወማል።እነዚህ ሃሳቦች በ2022 ውይይት ተደርጎባቸዋል። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እ.አ.አ በመጋቢት 2022 መጀመሪያ ላይ ሩሲያ የጠየቀችውን የደህንነት ዋስትና እንዳላገኘች በመግለጽ፤ ኔቶ ለሩሲያ ፍላጎት አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን ውድቅ እንዳደረገ አስታውቋል። ግሩሽኮ ስለ ኔቶ እና የአሜሪካ ጦር ከባልቲክ ቀጣና ለቆ የመውጣት ሃሳብን በተመለከት ሲናገሩ፤ ሩሲያ በምዕራቡ ዓለም ከሚደቀንባት ሥጋት አንጻር ትንቀሳቀሳልች ብለዋል፡፡"የአየር ማረፊያና የወደብ አውታር እየተስፋፋና እየተጠናከረ ነው። ኔቶ የመንቀሳቀስ አቅሙን ከፍ ለማድረግ አዲስ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ክፍሎችን እየፈጠረ ነው። የልምምድ እንቅስቃሴው በመጠንም፤ በስፋትም እየጨመረ እንደመጣ እያየን ነው። የበለጠ ጠበኛ እየሆኑ እና በተነፃፃሪ ጠላት (የሩሲያ ፌዴሬሽን) ላይ ያተኮረ ወታደራዊ ዘመቻ እያደረጉ ነው። ልንጋፈጠው የሚገባው እውነታ ይህ ነው" ሲሉ ባለስልጣኑ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን | X ላይ ይከተሉን
Sputnik
ሩሲያ በዩክሬን ግጭት አፈታት ሂደት ጠንካራ የደህንነት ዋስትና ትፈልጋለች ሲሉ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ አሌክሳንደር ግሩሽኮ ከኢዝቬስቲያ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ እነዚህ ዋስትናዎች የዩክሬንን ገለልተኝነት እና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ሀገራት ዩክሬንን የሕብረቱ አባል አድርጎ አለመቀበልን ማካተት አለባቸው ብለዋል። እ.አ.አ በ2021መገባደጃ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአሜሪካ እና ኔቶ የደህንነት ዋስትና የሚጠይቅ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ይፋ አድርጓል፡፡ ረቂቅ ሰነዱ የኔቶን ወደ ምስራቅ መስፋፋት፣ የዩክሬን ህብረቱን መቀላቀል እና እ.አ.አ ከ1997 ጀምሮ የተደረገውን የወታደሮች እና የጦር መሳሪያዎች መስፋፋት ይቃወማል።እነዚህ ሃሳቦች በ2022 ውይይት ተደርጎባቸዋል። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እ.አ.አ በመጋቢት 2022 መጀመሪያ ሩሲያ የጠየቀችውን የደህንነት ዋስትና እንዳላገኘች በመግለጽ፤ ኔቶ ለሩሲያ ፍላጎት አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን ውድቅ እንዳደረገ አስታውቋል። ግሩሽኮ ስለ ኔቶ እና የአሜሪካ ጦር ከባልቲክ ቀጣና ለቆ የመውጣት ሃሳብ ዙርያ ሲናገሩ፤ ሩሲያ በምዕራቡ ዓለም ከሚደቀንባት ሥጋት አንጻር ትንቀሳቀሳልች ብለዋል፡፡"የአየር ማረፊያና የወደብ አውታር እየተስፋፋና እየተጠናከረ ነው። ኔቶ የመንቀሳቀስ አቅሙን ከፍ ለማድረግ አዲስ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ክፍሎችን እየፈጠረ ነው። የልምምድ  እንቅስቃሴው በመጠንም፤ በስፋትም እየጨመረ እንደመጣ እያየን ነው። የበለጠ ጠበኛ እየሆኑ እና በተነፃፃሪ ጠላት (የሩሲያ ፌዴሬሽን) ላይ ያተኮረ ወታደራዊ ዘመቻ እያደረጉ ነው። ልንጋፈጠው የሚገባው እውነታ ይህ ነው" ሲሉ ባለስልጣኑ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን