የማዕድን ደንብ ጥሰዋል የተባሉ ሶስት የቻይና የነዳጅ ኩባንያ ተወካዮች ከኒጄር መባረራቸው ተነገረ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት የኒጄር መንግሥት በ2024 የወጣውን የማዕድን ደንብ ማሻሻያ ሕግ በመጣስ የቻይና ብሄራዊ ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን፣ ዚንደር የማጣሪያ ኩባንያ እና የምዕራብ አፍሪካ ጋዝ ፓይፕላየን ኩባንያን ከሀገሪቱ አባሯል። የኒጄር ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ኢብራሂም ሃሚዱ "ኩባንያዎቹ በተቻለ መጠን ኒጄራውያን ንዑስ ተቋራጮችን እንዲመርጡ እና አብዛኛዎቹ ንዑስ ተቋራጮች ቻይናውያን እንዳይሆኑ እንጠይቃለን" ማለታቸውን ዘገባቸውን አመላክተዋል።ኩባንያዎቹ ለሀገር ውስጥ ሠራተኞች ፍትሐዊ ክፍያ መክፈል፣ የሀገር ውስጥ አቅራቢዎችን የኮንትራት ኮታ ማክበር፣ ለሀገር ውስጥ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ቅድሚያ መስጠት፣ የኒጄሪያውያን ሠራተኞቻቸውን ክህሎት የሚያሻሽል ሥልጠና ማቅረብ፣ የእድገት እድል መስጠት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ አልቻሉም ነው የተባለው፡፡ በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia