የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አፍሪካ ሲዲሲን የበለጠ ለማሳደግ የአፍሪካ ሕብረት ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠየቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይህን ያሉት ከአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) ዋና ዳይሬክተር ዣን ካሴያ ጋር በድርጅቱ የአዲስ አበባ ዋና መሥሪያ ቤት ካደረጉት ውይይት በኋላ ነው። የአፍሪካ ሲዲሲ ላብራቶሪዎች እና የምርምር አቅም በሽታን ለመከላከል እና ለወረርሽኞች ምላሽ ለመስጠት ወሳኝ እንደሆኑ አበክረው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕከሉ አሠራሩን እንዲያሻሽል የአፍሪካ ሀገራት የበለጠ ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። ተቋሙን ይበልጥ ለማጠናከር ከውጭ ሀገራት ጋር ትብብር መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነም ተናግረዋል። የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዣን ካሴያ የአፍሪካ ሲዲሲ ዘላቂ የጤና መፍትሄዎችን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ እንደሆነ በድጋሚ አስገንዝበዋል። ℹ እ.አ.አ በ2016 ተመሥርቶ በ2017 በይፋ ሥራ የጀመረው አፍሪካ ሲዲሲ የአህጉሪቱን የህብረተሰብ ጤና በማሻሻል ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በቻይና ድጋፍ የተገነባው ዋና መሥሪያ ቤት በ2023 የተመረቀ ሲሆን፤ በዚያው ዓመት በቻይና የሚደገፍ የጥናትና ምርምር ላብራቶሪ ተከፍቷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia